Fana: At a Speed of Life!

አንጋፋው የማሲንቆና በገና ተጫዋች አለማየሁ ፋንታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አንጋፋው የማሲንቆና በገና ተጫዋች፣ ድምጻዊና የሙዚቃ መምህር አለማየሁ ፋንታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ግጥምና ዜማ በመድረስና ክራር በመጫወት የሚታወቁት አለማየሁ ፋንታ፤ ለበርካታ ዓመታት በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት በመምህርነት አገልግለዋል፡፡

በተለየ የማሲንቆ አጨዋወታቸው የሚታወቁ ሲሆን፤ በዓለም ዙሪያ የኢትዮጵያን ባህል ማስተዋወቅ ችለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት የአለማየሁ ፋንታን ህልፈት አስመልክቶ ባስተላለፈው የሀዘን መግለጫ መልዕክት፤ ለኢትዮጵያ የሙዚቃ ማህበረሰብና ለመላው ሕዝብ ከባድ ሀዘን ነው ብሏል፡፡

በነገው ዕለት የአስክሬን ሽኝት መርሐ-ግብር ተደርጎ የቀብር ሥነ ሥርዓት እንደሚፈጸምም ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.