Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከኮሪያ ሪፐብሊክ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

‎አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሥራና ክሕሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያ የኮሪያ ሪፐብሊክ አምባሳደር ጁንግ ካንግ ጋር በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

ሚኒስትሯ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መረጃ÷ ከአምባሳደር ጁንግ ካንግ ጋር ልህቀት ማምጣት በሚያስችሉ የክህሎት ልማት እንዲሁም የእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ሥራዎች ላይ በትብብር ለመሥራት ተግባብተናል ብለዋል፡፡

ኮሪያ በቴክኒክና ሙያ ዘርፉ ለኢትዮጵያ ጠንካራ ድጋፍ ከሚያደርጉ ሀገራት መካከል እንዷ መሆኗን ጠቅሰው÷ ትብብሩ ግንኙነቱን ወደላቀ ደረጃ እንደሚያሳድግ አመልክተዋል፡፡

ኢትዮጵያና ኮሪያ ዘመናትን የተሻገረ ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን በመጥቀስም የሁለቱን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት በማድረግ ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ላሳዩት ቁርጠኝነት ለአምባሳደሩ ምስጋና አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.