Fana: At a Speed of Life!

በታዳሽ ኃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በማስፋት የነዳጅ ወጪን መቀነስ እንደሚገባ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በታዳሽ ኃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በማስፋት የነዳጅ ወጪን መቀነስ እንደሚገባ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) አስገነዘቡ።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የኤሌክትሪክና ታዳሽ ኃይል ተጠቃሚ ተሽከርካሪዎች ሀገር አቀፍ ረቂቅ ስትራቴጂ ማዘጋጀታቸው ተገልጿል።

የአየር ብክለትን ለመቀነስ እና የከተሞችን ጽዳት ለመጠበቅ የነዳጅ መኪኖችን በመቀነስ አረንጓዴ ትራንስፖርትን ማበረታታት እንደሚገባም ያነሱት ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)፤ ለነዳጅ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ ወጪ መቀነስ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

በዚህም ለነዳጅ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ በመቀነስ ለሌላ የልማት ሥራ ማዋል እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

አሁን ላይ በታዳሽ ኃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ሙሉ ለሙሉ ወደ ሥራ ለማስገባት የተወሰኑ ተግዳሮቶች እንዳሉ ጠቁመዋል።

በታዳሽ ኃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ሙሉ ለሙሉ ወደ ሥራ ለማስገባት የህግ ማዕቀፎችን እና አሰራሮችን ማዘጋጀት እንዲሁም በየከተሞች የቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎችን ማስፋት ቀጣይ ሥራዎች መሆናቸውንም አስታውቀዋል።

በዘመን በየነ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.