Fana: At a Speed of Life!

በቴክኖሎጂ ዘርፍ በቢዝነስ የፈጠራ ሐሳብ ተወዳዳሪዎች እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለሁለት ወራት በቴክኖሎጂ ዘርፍ ባላቸው የቢዝነስ የፈጠራ ሐሳብ ላወዳደሯቸው ባለሙያዎች ዕውቅና ሰጡ፡፡

የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላን (ዶ/ር) ጨምሮ የፌደራል እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በዕውቅና አሰጣጥ በመርሐ-ግብሩ ላይ ተገኝተዋል።

በዚሁ ወቅት በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማሩ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት ከተያዘው ተልዕኮ አንጻር፤ ሚኒስቴሩ ለተመረጡ ስታርትአፕ ተወዳዳሪዎች ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱ ተገልጿል።

ባለፉት ሁለት ወራትም በባሕር ዳር ከተማ 28 የፈጠራ ሐሳቦች መወዳደራቸው እና በልየታው መስፈርት መሠረት ብቁ ሆነው የተገኙ ሦስት የፈጠራ ሐሳቦች የሥራ ማስጀመሪ የገንዘብ ሽልማት መሸለማቸው ተጠቅሷል፡፡

በደሳለኝ ቢራራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.