Fana: At a Speed of Life!

የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የሰላም አስከባሪ የሠራዊት አባላት እያስመረቀ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለሰላም ማስከበር ተልዕኮ ያሰለጠናቸውን የሰላም አስከባሪ የሠራዊት አባላት እያስመረቀ ነው።

እየተመረቁ የሚገኙት የሰላም አስከባሪ የሠራዊት አባላት የ20ኛ እና የ21ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃዎች ናቸው።

በሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የሥነ-ልቦና ግንባታ ኃላፊ ኮሎኔል በላይ ህሩይ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ተመራቂ የሠራዊት አባላቱ ለሰላም ማስከበር ተልዕኮ በውጭ ሀገር የሚሰማሩ ናቸው።

ሠራዊታችን ብቃትና ሕዝባዊ ወገንተኝነት አለው፤ ተቀባይነቱም በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ነው ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.