ከአነስተኛ ወደ ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች መስፈንጠር እንደሚቻል ከቬይትናም ተሞክሮ መቅሰም ተችሏል – ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከአንስተኛ ኢንዱስትሪዎች ወደ ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች መስፈንጠር እንደሚቻል ከቬይትናም ተሞክሮ መቅሰም መቻሉን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ገለጹ።
ቬይትናም በጥቂት ዓመታት ውስጥ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ከፍተኛ እመርታን ካስመዘገቡ ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗን የገለጹት ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር)፤ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በመሳብ አማራጭ የኢንቨስትመንት ማዕከል በመሆን ትልቅ ዕድገት ማስመዝገቧን ተናግረዋል።
በዚህም የአምራች ዘርፉ በኢኮኖሚው ውስጥ ያለው ድርሻ ከፍተኛ ሊሆን መቻሉን ገልጸዋል።
በዓለም አቀፍ የማኑፋክቸሪንግ እሴት ሰንሰለት ውስጥ የሚኖር ጂኦፖለቲካዊ አካሄዶችን በማየት የወሰዱት እርምጃዎቿ ትልቅ ትምህርት የተወሰደበት መሆኑን አንስተዋል።
እንዲሁም ከትናንሽ ኢንዱስትሪዎች ወደ ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች መስፈንጠር እንደሚቻልም ከቬትናም ተሞክሮ መቅሰም መቻሉን መግለጻቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
ኢንዱስትሪዎች በሀገር ውስጥ ግብአት እንዲጠቀሙ ክትትል እና ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።