ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ትንሳኤን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋሩ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ከሙሉ ፍቅርና ብርሃን ይሁን የሕጻናት መርጃ ተቋም ለተውጣጡ ከ100 በላይ ሕጻናት ማዕድ አጋሩ፡፡
በተጨማሪም ቀዳማዊት እመቤቷ ባስገነቡት የዘውዲቱ መሸሻ የሕጻናት ማሳደጊያ ማዕከል ድጋፍ ለሚደረግላቸው ሕጻናት እንኳን አደረሳችሁ በማለት ማዕድ ማጋራታቸው ተገልጿል፡፡
ከማዕድ ማጋራቱ ባሻገር ሕጻናቱ፤ በወዳጅነት ዐደባባይ (ፍሬንድሽፕ ፓርክ) በጨዋታና በመዝናናት ጊዜያቸውን ማሳለፋቸውን የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡