በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ ኤምባሲዎች ለትንሳዔ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የትንሳዔ በዓልን አስመልክቶ በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ ኤምባሲዎች ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በኢትዮጵያ የብሪታኒያ፣ አሜሪካ፣ ሩሲያ፣ ጀርመን፣ አውስትራሊያ እንዲሁም የፓኪስታን ኤምባሲዎች በዓሉ የፍቅር እና የደስታ እንዲሆን ተመኝተዋል።
ከኤምባሲዎቹ በተጨማሪ ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ የሆኑ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በዓሉን አስመልክቶ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።