Fana: At a Speed of Life!

የድሬዳዋ አስተዳደር የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋራ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የድሬዳዋ አስተዳደር የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋርቷል።

በመርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ባስተላለፉት መልዕክት፥ የመተጋገዝና የመረዳዳት እሴታችን ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

በድሬዳዋ የተለያዩ በዓላት በአንድነትና በመተጋገዝ እንደሚከበር ገልጸው፥ የትንሳኤ በዓልም በተመሳሳይ ሁኔታ እየተከበረ መሆኑን ተናግረዋል።

በድሬዳዋ በዓላት በፍቅርና አብሮነት መከበራቸው ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ጠቁመው፥ በዛሬው ዕለትም የተደረገው የዚሁ ማሳያ ነው ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.