Fana: At a Speed of Life!

በሥራ እና ክኅሎት ዘርፍ የተገኙ ውጤቶችን ለማላቅ ፈጠራን ማዕከል ያደረገ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሥራ እና ክኅሎት ዘርፍ የተገኙ ውጤቶችን ለማላቅ በትጋት፣ ፍጥነትና ፈጠራን ማዕከል ያደረገ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ።

የሥራ እና ክኅሎት ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች የተቋሙን የዘጠኝ ወራት የመንግስት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያይተዋል።፡

መድረኩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) በተገኙበት ነው የተካሄደው።

የሥራ እና ክኅሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ በመድረኩ የሀገር አቀፉን የዘጠኝ ወራት አፈፃፀምን ከዓለም አቀፉ ሁኔታ፣ ከማክሮ ኢኮኖሚ እና ከሪፎርም አፈፃፀምና አዝማሚያዎች ጋር በማስተሳሰር በዘላቂ ልማታችን ላይ ያለውን አንድምታ አይነተናል ብለዋል፡፡

የመሠረተ ልማት እና የፕሮጀክቶች አፈፃፀምን ጨምሮ ማህበራዊ አካታችነት እና ሁለተናዊ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የተሠሩ ሥራዎችን እና የተገኙ ውጤቶችን እንዲሁም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በዝርዝር መመልከታቸውንም ገልጸዋል፡፡

በተደረገው ሁሉን አቀፍ ርብርብ ተስፋ ሰጪና ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገቡን አመላክተዋል።

በቀሪ ወራት በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነትና የተቋም ግንባታ ጉዳዮች ላይ በዘርፉ የተገኙ ውጤቶችን ለማላቅ በትጋት ፍጥነትና ፈጠራን ማዕከል ያደረገ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባን ተግባብተናልም ነው ያሉት ሚኒስትሯ፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ውይይቱን በመምራት ለቀጣይ ሥራዎች መነሳሳትን የሚፈጥር ግብዓት በመስጠታቸውም ምስጋና አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.