Fana: At a Speed of Life!

በወንዶች የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል አትሌት ሳሙኤል ፍሬው አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በወንዶች የ3 ሺህ ሜትር የመሰናክል ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ሳሙኤል ፍሬው አሸንፏል።

በቻይና ዢያሚንግ ውድድር አትሌት ሳሙኤል በ8:05.61 በመግባት የቦታው ክብረወሰንና የዓመቱ የርቀቱ ፈጣን ሠዓት በማስመዝገብ በድንቅ ብቃት በበላይነት ማሸነፍ ችሏል።

ሞሮኳዊው የኦሎምፒክ ሻምፒዮን አትሌት ኤልባካሊን ሁለተኛ እንዲሁም ኬንያዊ ሲሞን ኮኤች ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቃቸውን የአትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል።

በተያያዘ መረጃ ቀደም ብሎ በተደረገ የሴቶች የ5 ሺህ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ2ኛ እስከ 7ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።

በውድድሩ ኬንያዊቷ አትሌት ቢያትሪስ ቺቤት የቦታውን ክብረ ወሰን በማሻሻል ስታሸንፍ ኢትዮጵያውቷ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ የዓመቱን የግል ምርጥ ስዓቷን በማስመዝገብ ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቃለች።

አትሌት ብርቄ ኀየሎም እና አትሌት ሂሩት መሸሻ 3ኛ እና 4ኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቅ ችለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.