Fana: At a Speed of Life!

ሕብረተሰቡ ከፖሊስ ጋር የሚያደርገው ትብብር እንዲጠናከር ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፖሊስ ተቋም ላለፉት ዓመታት ሀገርን ለማፅናት፣ ሰላምና ደኅንነትን ለማስጠበቅ መስዋዕትነት መክፈሉን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ከሚሽን ኮሚሽነር ፍስሐ ጋረደው ገለፁ፡፡

116ኛው የፖሊስ ምሥረታ በዓል ”የተለወጠ ሀገር ያደገ ፖሊስ” በሚል መሪ ሐሳብ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ ተከብሯል፡፡

ኮሚሽነር ፍስሐ በዚሁ ወቅት የፖሊስ ሥራ ስኬት ከሕብረተሰቡ ተሳትፎ ጋር የተቆራኘ መሆኑን በመግለጽ፤ ይህ ቅንጅት እንዲጠናከር ጠይቀዋል፡፡

በቀጣይም ከሕዝቡ ጋር በመተባበር የሀገርን ሰላም በማይናወጥ መሠረት ላይ ለማቆም እንደሚሠራ አስገንዝበዋል፡፡

የወላይታ ዞን የመንግሥት ረዳት ተጠሪ መስፍን ቶማስ በበኩላቸው፤ ፖሊስ ከራሱ በፊት ሀገርንና ሕዝብን የሚያስቀድም መሆኑን በመገንዘብ ክብር መስጠት እንደሚገባ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

ፖሊስ ከሕዝቡ ጋር ተባብሮ ባከናወናቸው ሥራዎችም አስተማማኝ ሰላም እና ደኅንነት መስፈኑን አረጋግጠዋል፡፡

በመለሰ ታደለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.