Fana: At a Speed of Life!

የሻምፒየንስ ሊጉ የሳምንቱ ምርጥ 11

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሳምንቱ አጋማሽ በተከናወኑ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች ፒኤስጂ አርሰናልን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ፥ ባርሴሎና ከኢንተር ሚላን 3 ለ 3 አቻ ተለያይተዋል፡፡

በሁለቱ ጨዋታዎች ድንቅ የነበሩ 11 ተጫዋቾች በአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ይፋ ተደርገዋል፡፡

በግብ ጠባቂነት ጣሊያናዊው የፒኤስጂ ግብ ጠባቂ ዶናሩማ ሲመረጥ፥ የቡድን አጋሩ ማርኪንዮስ እና የ37 ዓመቱ የኢንተር ሚላን ተከላካይ ፍራንቼስኮ አቼርቢ በመሃል ተከላካይነት ተካትተዋል፡፡

ወጣቱ የአርሰናል ተከላካይ ሊውስ-ስኬሊ በግራ መስመር እንዲሁም ዴንዘል ዱምፍሪስ ከኢንተር ሚላን በቀኝ መስመር ተከላካይነት ተመርጠዋል፡፡

በአማካይ ስፍራ ፔድሪ ከባርሴሎና፣ ቪቲንሃ ከፒኤስጂ እንዲሁም ባሬላ ከኢንተር ሚላን በሳምንቱ ምርጥ 11 ስብስብ የተካተቱ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

ፒኤስጂ ከሜዳው ውጭ አርሰናልን ባሸነፈበት ጨዋታ ብቸኛዋን ጎል ያስቆጠረው ኦስማን ዴምቤሌ እንዲሁም የባርሴሎናዎቹ ራፊኒሃ እና ላሚን ያማል በ4-3-3 አሰላለፍ በፊት መስመር ተመርጠዋል፡፡

ፒኤስጂ 4 ተጫዋቾችን በማስመረጥ ቀዳሚ ሲሆን፥ ኢንተር ሚላን እና ባርሴሎና እያንዳንዳቸው ሦስት ተጫዋቾችን እንዲሁም አርሰናል አንድ ተጫዋች አስመርጠዋል፡፡

በኃይለማሪያም ተገኝ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.