Fana: At a Speed of Life!

በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ከ7 ሺህ 900 በላይ ት/ቤቶች ተገነቡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ከ7 ሺህ 900 በላይ ትምህርት ቤቶች ግንባታ መጠናቀቁን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በሚኒስቴሩ የትምህርት ፕሮግራሞችና ጥራት ማሻሻያ ሃላፊ ዳዊት አዘነ እንዳሉት÷በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ 50 ሺህ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት ከደረጃ በታች ናቸው።

ከደረጃ በታች የሆኑ ት/ቤቶችን ለማሻሻልና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ እስካሁን ከ7 ሺህ 900 በላይ የቅድመ መደበኛ፣ 1ኛ ደረጃ እና 2ኛ ደረጃ አዳዲስ ት/ ቤቶች ተገንብተዋል ነው ያሉት፡፡

በተመሳሳይ በንቅናቄው የ29 ሺህ 900 ት/ቤቶች እድሳት እና ጥገና ሥራ መከናወኑን ሃላፊው ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ገልጸዋል፡፡

ሕብረተሰቡ ንቅናቄውን ለማሳካት በጉልበት፣ በእውቀትና በገንዘብ የሚያደርገው ተሳትፎ የሚበረታታ እንደሆነም ጠቅሰዋል፡፡

የትምህርት ጥራት ችግርን ለመቅረፍ ከታች ከመሰረቱ በትኩረት መሰራት እንዳለበት አቅጣጫ መቀመጡንም አስገንዝበዋል፡፡

በመሳፍንት እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.