Fana: At a Speed of Life!

ሀገር በቀል ቴክኖሎጂን ለሀገር ብልጽግና ለማዋል ዘርፉን መደገፍ ይገባል – አቶ ደስታ ሌዳሞ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገር በቀል ቴክኖሎጂን ለሀገር ብልጽግና ለማዋል ዘርፉን በትኩረት መደገፍ ይገባል ሲሉ የሲዳማ ከልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት÷የኢንዱስትሪ ሽግግርን በማፋጠን ከውጪ በምንዛሪ የሚገቡ ቴክኖሎጂዎችን በሀገር ውስጥ ለመተካት የተጀመረው እንቅስቃሴ የሚበረታታ ነው፡፡

የክልሉ መንግስት ቴክኒክ ኮሌጆችንና የሥራ ፈጠራ ባለቤቶችን በስልጠና እንዲሁም መነሻ ካፒታል በመስጠት ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በክልሉ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ዘመን ተሻጋሪ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር ረገድ እያሳዩት ያለው ውጤት ከፍተኛ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በተለይም በሃዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተሰሩ የእህል መውቂያና የፕላስቲክ ማቀነባበሪያ ማሽኖች የአርሶ አደሩን እንግልት የሚቀንሱ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

ተሞክሮው በቀጣይ ሌሎች ማሽኖችን ማምረት የሚያስችል ክህሎት መኖሩን የሚያመላክት መሆኑን የክልሉ ሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሃገረጺዮን አበበ ተናግረዋል፡፡

ዘርፉን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ግንዛቤና የገበያ ትስስር ላይ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው÷ለአብነትም ለ29 ሺህ ወጣቶች ሥልጠና መሰጠቱን ጠቅሰዋል፡፡

በጥላሁን ይልማ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.