Fana: At a Speed of Life!

የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው- ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የትምህርት ጥራት እና ተደራሽነትን ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ፡፡

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ትምህርት ሚኒስቴር ከሚያስገነባቸው ሞዴል 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ውስጥ አንዱ የሆነውን አጋ ጢንጠኖ ሞዴል 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ በጉጂ ዞን ሻኪሶ ከተማ አስጀምረዋል፡፡

በዚህ ወቅትም የትምህርት ሥርዓትን ከመሠረቱ በመቀየር ሀገር የሚገነባ ቀጣይ ትውልድ ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ትምህርት ቤቱ በ500 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የሚገነባ መሆኑን ጠቁመው÷ ግንባታው በ12 ወራት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ አመልክተዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ም/ሃላፊ ገላና ወ/ሚካኤል (ዶ/ር) በበኩላቸው ÷ የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ በሳይንስና ቴክኖሎጂ የዳበሩ የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጎችን ለማፍራት በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡

በክልሉ በትምህርት ሚኒስቴር አማካኝነት የተጀመሩ ሞዴል 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ግንባታ ጥራታቸውን ጠብቀው በተያዘላቸው ጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

በፀሃይ ጉሉማ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.