Fana: At a Speed of Life!

የጋሸና-ላሊበላ-ብልባላ-ሰቆጣ አስፋልት መንገድ ግንባታ ዳግም ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ግንባታው ተቋርጦ የቆየውን የጋሸና-ላሊበላ-ብልባላ-ሰቆጣ የአስፋልት መንገድ ግንባታ በዛሬው ዕለት አስጀምረዋል።

204 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክቱ ለአካባቢው ማሕበረሰብ ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንደሚያስገኝ ተመላክቷል።

የኢንዱስትሪ ውጤቶችን ከዋና ዋና የክልሉ ከተሞች ወደ አካባቢው ለማስገባትና የግብርና ምርቶችን ደግሞ ወደ መሃል ሀገር ለመላክ ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥርም ተገልጿል።

የመንገዱን ግንባታ በማስቀጠል ቀሪ ሥራዎችን ለማጠናቀቅ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር 5 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በጀት እንደተያዘ መጠቆሙን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.