Fana: At a Speed of Life!

ፋና ላምሮት የምዕራፍ 19 የፍጻሜ ውድድር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለሶስት ወራት በጠንካራ ፉክክር ሲካሄድ የቆየው ፋና ላምሮት የምዕራፍ 19 የፍጻሜ ውድድር በደማቅ ሥነ ሥርዓት መካሄድ ጀምሯል፡፡
ለፍጻሜ የደረሱት አራቱ ተወዳዳሪዎች ብሩክ ሰለሞን፣ ዮሴፍ ጉልላት፣ ካሳሁን ዘውዱ እና ኤፍሬም ጌታቸው ብርቱ ፉክክር እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
ተወዳዳሪዎቹ በሶስት ዙር የመረጧቸውን ሙዚቃዎች ከኮከብ ባንድ ጋር እያቀረቡ ሲሆን፤ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ለተወዳዳሪዎቹ የ1 ሚሊየን ብር ሽልማት አዘጋጅቷል።
ለ5ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በቀጥታ ማለፋቸውን ባለፈው ሳምንት ያረጋገጡት ተወዳዳሪዎቹ፤ 1ኛ ደረጃን የሚያገኝ 400 ሺህ ብር፣ 2ኛ ደረጃ 300 ሺህ ብር፣ 3ኛ ደረጃ 200 ሺህ ብር እንዲሁም 4ኛ ደረጃን የሚያገኝ 100 ሺህ ብር ሽልማት ይበረከትለታል።
አድማጭ ተመልካቾች የፍጻሜ ውድድሩን በሁለቱም የፋና ቴሌቪዥን ቻናሎች፣ በፋና ኤፍኤም 98 ነጥብ 1 እና በክልል ኤፍኤሞች፣ በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የዲጂታል ሚዲያ አማራጮች በቀጥታ መከታተል ይችላሉ፡፡
ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አድማጭ ተመልካቾች የሚገለፀውን የተወዳዳሪዎች ኮድ በ8222 አጭር የጽሑፍ መልዕክት በመላክ እየተዝናኑ እንዲደግፉ ይጋብዛል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.