የአርበኞች መታሰቢያ ቀን ምክንያት በማድረግ በነገው ዕለት 21 ጊዜ መድፍ ይተኮሳል
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በነገው ዕለት የሚከበረውን የአርበኞች መታሰቢያ ቀን ምክንያት በማድረግ መድፍ እንደሚተኮስ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ ለፋና ዲጂታል እንዳስታወቀው÷ የአርበኞች መታሰቢያ ቀንን ምክንያት በማድረግ ነገ ሚያዝያ 27 ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ 21 ጊዜ መድፍ ይተኮሳል፡፡