ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮ ኤሌክትሪክን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የቅዱስ ጊዮርጊስን ብቸኛ ግብ አማኑኤል ኤርቦ ከመረብ አሳርፏል፡፡
የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል ቀን 9 ሰዓት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ምሽት 12 ሰዓት ስሑል ሽረ ከፋሲል ከነማ ይጫወታሉ፡፡