Fana: At a Speed of Life!

ፒኤስጂ ከአርሰናል ለሙኒኩ ፍጻሜ….

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ በግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ ፒኤስጂ በሜዳው ፓርክ ደ ፕሪንስ ዛሬ ምሸት 4 ሰዓት ላይ አርሰናልን ያስተናግዳል።
የዛሬ ምሽት የግማሽ ፍጻሜ ተፋላሚ ቡድኖች በታሪካቸው አንድም ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን አሳክተው አያውቁም።
ሁለቱ ቡድኖች ኤሚሬትስ ላይ ባደረጉት የመጀመሪያ ዙር የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ በኦስማን ዴምቤሌ ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፉ ይታወሳል።
የፈረንሳይ ሊግ ኧ ዋንጫን አስቀድሞ ማንሳቱን ያረጋገጠው ፒኤስጂ በሳምንቱ መጨረሻ ለወሳኝ ተጫዋቾቹ እረፍት ሰጥቶ በሊጉ ሽንፈት አስተናግዷል።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በበኩሉ በሳምንቱ መጨረሻ ባደረገው የሊጉ ጨዋታ ወሳኝ ተጫዋቾቹን ይዞ ቢገባም ድል ማድረግ አልቻለም።
የፒኤስጂው አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ከጨዋታው አስቀድሞ በሰጡት አስተያየት፥” ግማሽ ፍጻሜ ላይ የደረስነው ስለሚገባን ነው፤ የመጀመሪያውን ዙር አሸንፈናል፤ ዛሬም አላማችን ማሸነፍ ነው ብለዋል።
የመድፈኞቹ አለቃ ሚኬል አርቴታ በበኩላቸው ፥ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች በተጫዋቾች ላይ ከፍተኛ ብስጭት እና ንዴት ተፈጥሯል፤ ቁጭቱን ለዛሬው ጨዋታ መጠቀም አለብን ነው ያሉት።
ፓርክ ደ ፕሪንስ ስታዲየም ላይ የሚደረገውን ተጠባቂ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ ጀርመናዊው ዳኛ ፌሊክስ ዝዋየር በመሐል ዳኝነት ይመሩታል።
ዋና ዳኛው ከዚህ በፊት በጨዋታ ማጭበርበር ተከሰው ለስድስት ወራት ከዳኝነት ታግደው እንደነበር አይዘነጋም።
የሁለቱ ቡድኖች የድምር ውጤት አሸናፊ በፍጻሜው ከጣልያኑ ክለብ ኢንተርሚላን ጋር በአሊያንዝ አሬና ስታዲየም የሚፋለም ይሆናል።
በወንድማገኝ ጸጋዬ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.