Fana: At a Speed of Life!

ወላይታ ድቻ አርባምንጭ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ28ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ወላይታ ድቻ አርባምንጭ ከተማን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የወላይታ ድቻን የማሸነፊያ ግቦች ሙሉቀን አዲሱ እና ካርሎስ ዳምጠው ሲያስቆጥሩ፤ የአርባምንጭ ከተማን ብቸኛ ጎል አህመድ ሁሴን ከመረብ አሳርፏል፡፡

ወላይታ ድቻ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ወደ ድል ሲመለስ አርባ ምንጭ ከተማ በበኩሉ ባለፉት አምስት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ወላይታ ድቻ በ41 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፤ አርባምንጭ ከተማ በ35 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.