Fana: At a Speed of Life!

ማንቼስተር ዩናይትድ ከአትሌቲክ ቢልባኦ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዩሮፓ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ በሜዳው ኦልድትራፎርድ ምሽት 4 ሠዓት ላይ አትሌቲክ ቢልባኦን ያስተናግዳል።

በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ ወደ ስፔን አቅንቶ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፉ ይታወሳል።

በሌላ በኩል ሁለቱ ቡድኖች በሳምንቱ መጨረሻ በየሊጋቸው ባደረጉት ጨዋታ ድል ማድረግ አልቻሉም።

የዛሬ የግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚዎቹ ከዚህ ቀደም በሁሉም ውድድር ሰባት ጊዜ የተገናኙ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ሁለቱም ሦስት ጊዜ ድል ሲቀናቸው አንድ ጊዜ አቻ ተለያይተዋል።

የማንቼስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ከጨዋታው አስቀድሞ በሰጡት አስተያየት፤ “በታሪክ አስከፊ በሆነብን በዚህ ዓመት የዩሮፓ ሊግ ዋንጫ ይዘን ልናጠናቅቅ እንችላለን፤ ነገርግን የሚቀይረው ነገር የለም ዓመቱ የሚያበሳጭ ነበር”  ብለዋል፡፡

አትሌቲክ ቢልባኦ ዛሬ ከማንቼስተር ዩናይትድ ጋር በሚያደርገው የዩሮፓ ሊግ ጨዋታ የወሳኝ ተጫዋቾቹን የኒኮ ዊሊያምስ፣ ኢናኪ ዊሊያምስ እና ሳንሴትን ግልጋሎት አያገኝም።

በሌላ የዩሮፓ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ በተመሳሳይ 4 ሠዓት ላይ ቶተንሃም ሆትስፐር ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ከቦዶ ግሊምት ጋር ጨዋታውን ያደርጋል።

በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ቶተንሃም ሆትስፐር 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፉ ይታወሳል።

በወንድማገኝ ፀጋዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.