የቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ቀን እየታሰበ ነው
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በአዳማ ከተማ የእግር ጉዞን ጨምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች እየታሰበ ነው፡፡
ቀኑ በየዓመቱ ሚያዝያ 30 የሚታሰብ ሲሆን፤ ዘንድሮም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ78ኛ በኢትዮጵያ ለ67ኛ ጊዜ “ሰብዓዊነትን እናፅና” በሚል መሪ ሐሳብ እየታሰበ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ሥራ አስፈፃሚዎች፣ ሠራተኞች፣ በጎ ፈቃደኞችና የአጋር አካላት ተወካዮችን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በአንዱዓለም ተስፋዬ