ዕዙ ተሞክሮውን ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ በሚያስችል መልኩ የምስረታ በዓሉን ያከብራል – ሌ/ጄ መሰለ መሠረት
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የምዕራብ ዕዝ የተጋድሎ ተሞክሮውን ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ በሚያስችል መልኩ 47ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እንሚያከብር የዕዙ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል መሰለ መሠረት ገለጹ።
የዕዙን የምስረታ በዓል አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት ሌ/ጄ መሰለ፤ ሠራዊታችን የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት እየተወጣ ነው ብለዋል።
የዕዙ የምስረታ በዓል የሚከበረው ተጋድሎውን ለተተኪው ትውልድ ሰንዶ ማስቀመጥ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነ ተናግረዋል።
በዚህም የዕዙ ነባር ኃይል ያለፈበትን ተሞክሮ እንዲያስታውስ የሚደረግ መሆኑን ጠቅሰው፤ አዲስ የተቀላቀለው ኃይል ዕዙ ካለፈበት ታሪክ ልምድ ወስዶ ጥንካሬውን እንዲያስቀጥል የሚያስችል እንደሆነም አስገንዝበዋል።
ሕዝባዊነታችንን ጠብቀን እየሄድን ነው፣ የህዝብ ድጋፍ አልተለየንም በማለት ገልጸው፤ በዓሉ ከህዝቡ፣ ከሌሎች ዕዞች እና ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመሆን እንደሚከበርም ጠቁመዋል።
በዮናስ ጌትነት