Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ታዬ በሩሲያ የድል በዓል የመሪዎች የእራት ግብዣ ላይ ተሳተፉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በ80ኛው የሩሲያ የድል በዓል ለሚሳተፉ የሀገራት መሪዎች በክሬምሊን ቤተመንግስት በተካሄደው የአቀባበልና የእራት ግብዣ ስነስርዓት ላይ ተሳትፈዋል።

የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በድል ቀን በዓል ላይ ለመሳተፍ ለመጡ የሀገራት መሪዎች አቀባበል አድርገዋል።

በስነስርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካና የሌሎች ሀገራት መሪዎች መሳተፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የድል በዓሉ 2ኛው የዓለም ጦርነት ማብቃቱን ተከትሎ በተለይም የቀድሞው ሶቪየት ኅብረት ጦር የተቀዳጀውን ድል በማሰብ በሞስኮ የቀይ አደባባይ የሚካሄደውን ከፍተኛ ወታደራዊ ትርኢት ጨምሮ ሌሎች መርሃ ግብሮች ይከናወናሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.