Fana: At a Speed of Life!

የወል ትርክትን ለማስረጽ የኪነ-ጥበብ ሚና ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከነጠላ ትርክት ይልቅ የወል ትርክት እንዲስፋፋና ሀገርም በዚሁ ላይ መሠረቷን እንድትጥል የኪነ-ጥበብ ሚና ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ፡፡

42ኛው ጉሚ በለል “ኪነ-ጥበብ ለኅብረ ብሔራዊ ሀገረ መንግሥት ግንባታ” በሚል መሪ ሐሳብ የኦሮሚያ ክልል አመራሮችን ጨምሮ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በተገኙበት እየተካሄደ ነው፡፡

የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ኃይሉ አዱኛ በዚሁ ወቅት፤ በኢትዮጵያ የሀገረ መንግሥት ግንባታ ውስጥ ኪነ-ጥበብ ከፍተኛ ሚና ሲጫወት መቆየቱን አውስተዋል፡፡

በተለይም የሀገርን ፍቅር ከማጉላት፣ ታሪክን በጥበብ ከማስተዋወቅ፣ የማኅበረሰብን የእርስበርስ ትስስር ከማጎልበትና የሀገርን ፀጋ ከማስተዋወቅ አንፃር ሚናው የጎላ እንደነበር አብራርተዋል፡፡

አሁንም መንግሥት ከነጠላ ትርክት ይልቅ የወል ትርክት እንዲስፋፋና ሀገርም በዚሁ ላይ መሠረቷን እንድትጥል እየሠራ መሆኑን አስታውሰው፤ ኪነ-ጥበብም በዚህ ላይ ከፍተኛ ሚና እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.