Fana: At a Speed of Life!

የ12ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ይሰጣል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈታናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን፤ በበይነ መረብ ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች በሁለት ዙር እንደሚፈተኑ ተናግረዋል፡፡

ይህም የሆነበት ዋናው ምክንያት በበይነ መረብ የመፈተን አቅምን ለመጨመር እና ያለውን የመሰረተ ልማት አቅም ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ፈተናው በ2 ዙር በበይነ መረብ መሰጠቱ ከመኖሪያ ቤታቸው እየተመላለሱ በበይነ መረብ የሚፈተኑ ተማሪዎችን ቁጥር ይጨምራል ብለዋል፡፡

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና 608 ሺህ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ገልጸው፤ ፈተናውን በወረቀት የሚወስዱ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ በዩኒቨርሲቲዎች የሚፈተኑ መሆኑን ጠቁመዋል።

ፈተናውን በበይነ መረብ የሚወስዱት ደግሞ በዩኒቨርሲቲዎች፣ በመንግስት እና በግል ትምህርት ቤቶች፣ በጤና እና መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ ባሉ ኮምፒዩተሮች ይፈተናሉ ብለዋል።

በመሳፍንት እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.