የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት 5 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ለመቄዶንያ አበረከተ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከአመራሩና ከሠራተኛው የሰበሰበውን 5 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ለመቄዶንያ የአረጋውያን እና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል አበረከተ።
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች በዛሬው ዕለት የመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከልን በመዘዋወር ተመልክተዋል።
በወቅቱም ከአገልግሎቱ አመራሮችና ሠራተኞች የተሰበሰበውን የ5 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለማዕከሉ መሥራች አቶ ቢኒያም በለጠ አስረክበዋል።
የአገልግሎቱ ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በወቅቱ እንደገለጹት፤ ማዕከሉ ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነትን ወስዶ የሰብዓዊ ተግባር የሚፈጽም ባለውለታ ድርጅት ነው።
ሁሉም ኢትዮጵያዊ በበጎ ተግባሩ እንዲሳተፍም መልዕክት ማስተላለፋቸውን አገልግሎቱ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የላከው መረጃ አመላክቷል።
በመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ድጋፍ የሚደረግላቸው አረጋውያን ለተደረገው እገዛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡