Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በጋሞ ዞን በመሬት ናዳ በደረሰው ጉዳት ሀዘናቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተው የመሬት ናዳ እና የጎርፍ አደጋ በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ በደረሰው ጉዳት የተሰማኝን ጥልቅ ልባዊ ሐዘን ለመግለፅ እወዳለሁ ብለዋል።

በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው የተጎጂ ቤተሰቦችና ዘመድ ወዳጆች መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡

በቀጣይም በአደጋው ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች መልሶ ለማቋቋምና የጉዳቱን ሰለባዎች ለመርዳት መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.