ከ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ከብክነት ማዳን መቻሉ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአስቸኳይ ሙስና መከላከል ሥራ ከ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ የሕዝብና መንግሥት ሃብት ከብክነት ማዳን መቻሉን የፌዴራል ሥነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ገለጸ፡፡
በኮሚሽኑ የሙስና መከላከል ጥናት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ገዛኸኝ ጋሻው እንዳሉት፤ በትውልድ ግንባታ ትምህርትና ስልጠና፣ በተቋማት አሠራር ሥርዓት ጥናትና የሕግ ተጠያቂነትን ለማስፈን ከተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሠራ ነው፡፡
በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ከክልል የሥነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽነሮች ጋር የአፈፃጸም ግምገማ መካሄዱን ጠቅሰው፤ ከ500 በላይ የአስቸኳይ ሙስና መከላከል ሥራ መከናወኑን ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡
በዚህም ከ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር እና 190 ሚሊየን ካሬ ሜትር የከተማና ገጠር መሬት ከብክነት ማዳን ተችሏል ብለዋል፡፡