Fana: At a Speed of Life!

47ኛ ዓመት የምዕራብ ዕዝ የምሥረታ በዓል በነቀምቴ ከተማ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የምዕራብ ዕዝ የተመሰረተበት 47ኛ ዓመት በዓል በኦሮሚያ ክልል በነቀምቴ ከተማ ወለጋ ስታዲየም እየተከበረ ነው።

በአከባበር ሥነ-ሥርዓቱ ላይ፤ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው ታደሠ እና የዕዙን ጨምሮ የሠራዊቱ ከፍተኛ መኮንኖች ተገኝተዋል፡፡

በተጨማሪም የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መሥተዳደር አሻድሊ ሃሰን፣ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድርና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፣ የሠራዊቱ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የዕዙ የምስረታ በዓል የሚከበረው ተጋድሎውን ለተተኪው ትውልድ ሰንዶ ማስቀመጥ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነ የምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጀኔራል መሠለ መሰረት መግለጻቸው ይታወሳል።

በዚህም የዕዙ ነባር ኃይል ያለፈበትን ተሞክሮ እንዲያስታውስ ለማድረግ፤ አዲስ የተቀላቀለው ኃይል ዕዙ ካለፈበት ታሪክ ልምድ ወስዶ ጥንካሬውን እንዲያስቀጥል በሚያስችል መልኩ የምስረታ በዓሉ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል።

ዕዙ ‘የጽናት ተምሳሌት፤ የኢትዮጵያ ጋሻ’ በሚል መሪ ሀሳብ ነው የምስረታ በዓሉን እያከበረ የሚገኘው።

በገላና ተስፋ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.