Fana: At a Speed of Life!

ፋይዳ ለኢትዮጵያ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብሔራዊ መታወቂያን ግንዛቤ ማሻሻልን አላማው ያደረገው የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ዛሬ በመስቀል አደባባይ ተደርጓል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ ባስጀመሩት በዚህ ውድድር 25 ሺህ ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን ከ400 በላይ አትሌቶች የተሳተፉበት ውድድር በሁለቱም ጾታ ተደርጓል።

በወንዶቹ ውድድር ይስማው ድሉ በበላይነት ሲያጠነቅቅ፣ ይበልጣል ጋሻው እና ንብረት ክፍሌ ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል።

በሴቶቹ ውድድር ደግሞ ዮርዳኖስ ጽጋብ፣ ንግስቲ ጎላ እና ይርጋለም ኪዳኔ ከአንድ እስከ ሶስት በመውጣት አሸንፈዋል።

በተጨማሪም የአካል ጉዳተኞች የሩጫ ውድድር በእለቱ የተደረገ ሲሆን በውድድሩ ያሸነፉ አትሌቶች የ50 ሺህ የ25 ሺህ እና የ15 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

የዝግጅቱ የክብር እንግዳ አንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ÷ ብሔራዊ መታወቂያ በሌሎች ሀገራት የተለመደ እና በርካታ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን አንስቷል።

በኢትዮጵያም ሁሉም ዜጋ የፋይዳ መታወቂያ ሊኖረው እንደሚገባ አመልክቷል።

በኢትዮጵያ እስካሁን 14 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ባለቤት ሆነዋል።

በትዝታ ወንድሙ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.