ማንቼስተር ዩናይትድ 17ኛ ሽንፈቱን አስተናገደ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ዩናይትድ በ2024/25 የውድድር ዘመን 17ኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል፡፡
በኦልድትራፎርድ ዌስትሃም ዩናይትድን ያስተናገደው ዩናይትድ ጃሮድ ቦውን እና ቶማስ ሱቼክ ባስቆጠሯቸው ግቦች 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡
በሌሎች የሊጉ 36ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጨዋታዎች ክሪስታል ፓላስ ቶተንሃምን 2 ለ 0 ሲያሸነፍ ኖቲንግሃም ፎረስት ከሌስተር ሲቲ 2 አቻ ተለያተዋል፡፡