Fana: At a Speed of Life!

ባርሴሎና ሪያል ማድሪድን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ35ኛ ሳምንት የስፔን ላሊጋ ጨዋታ ባርሴሎና ሪያል ማድሪድን 4 ለ 3 በሆነ ውጤት በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል፡፡

በጨዋታው ለባርሴሎና ራፊንሀ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ላሚን ያማል እና ኤሪክ ጋርሺያ  ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

ሪያል ማድሪድን ከሽንፈት መታደግ ያልቻሉ ሶስት ግቦች ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪልያን ምባፔ አስቆጥሯል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ባርሴሎና ሊጉን በ82 ነጥብ ሲመራው ሪያል ማድሪድ በ75 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

ባርሴሎና በዚህ የውድድር ዓመት በሁሉም ውድድር ባደረጓቸው አራት የእርስ በርስ ጨዋታዎች አራቱንም በማሸነፍ ሪያል ማድሪድ ላይ የበላይ መሆን ችሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.