ሐዋሳ ከተማ አርባምንጭ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ29ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሐዋሳ ከተማ አርባምንጭ ከተማን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የሐዋሳ ከተማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ እስራኤል እሸቱ በመጀመሪያው አጋማሽ ከመረብ አሳርፏል፡፡
ሐዋሳ ከተማ ተከታታይ ሁለተኛ ድሉን ሲያሳካ፤ አርባምንጭ ከተማ ደግሞ ባለፉት ሦስት ተከታታይ ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግዷል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ሐዋሳ ከተማ በ34 ነጥብ 12ኛ እንዲሁም አርባምንጭ ከተማ በ35 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
በዕለቱ የመጨረሻ መርሐ ግብር 12 ሠዓት ላይ በተረደገ ጨዋታ፤ ሲዳማ ቡና ኢትዮ ኤሌክትሪክን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡
ግቦቹንም ሀብታሙ ታደሰ እና ይገዙ ቦጋለ ለሲዳማ ቡና እንዲሁም አቤል ሀብታሙ ለኢትዮ ኤሌክትሪክ አስቆጥረዋል፡፡