3ኛው ዓለም አቀፍ የሰላም፣ የአብሮነትና የልማት ጉባኤ መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዛሬ እና ነገ በአዲስ አበባ ከተማ የሚካሄደው 3ኛው ዓለም አቀፍ የሰላም፣ የአብሮነትና የልማት ጉባኤ መካሄድ ጀመረ።
ጉባኤው በዋናነት የአፍሪካ የእምነት ማህበረሰብ ዘላቂ የልማት ግቦች ስኬትን ማፋጠን፣ የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 ለማሳካት እና የአፍሪካ የ2025 የቡድን 20 ሂደት መሳካትን ትኩረት አድርጎ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።
በጉባኤው ላይ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሃሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሃፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣ የጂ20 ኢንተር ፌዝ ፎረም ፕሬዚዳንት ደብሊው ኮል ዱርሃም (ፕ/ር) እንዲሁም የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እየተሳተፉ ነው።
ጉባኤው ከጂ20 ኢንተር ፌዝ ፎረም፣ ከአፍሪካ ህብረትና በአፍሪካ ህብረት ስር ከሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ጋር በትብብር የተዘጋጀ ነው።
በእዮናዳብ አንዷለም