Fana: At a Speed of Life!

ቀጣናዊ ደኅንነትን ለማስጠበቅ የጸጥታ ተቋማትን ማጠናከር አስፈላጊ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በምስራቅ አፍሪካ ያለውን ቀጣናዊ ደኅንነት ለማስጠበቅ ቀጣናዊ የጸጥታ ተቋማትን ማጠናከር እና በትብብር መስራት አስፈላጊ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ፡፡

የአፍሪካ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ኮሚቴ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ስብሰባ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም የሚረጋገጠው መተማመንን በመገንባት፣ በጋራ እድሎቻችን ላይ በመሥራት እና በማፅናት ነው ብላ እንደምታምንም ተናግረዋል፡፡

የአጀንዳ 2063 ግብ ሰላማዊ፤ግጭት የሌለባት እና የእድገት እድሎች የሰፉባት አፍሪካን እውን የማድረግ አጀንዳ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለአካባቢ ሰላም ለዓመታት በፅናት የቆመች ሀገር መሆኗን አንስተው ይህ የኢትዮጵያ የማይናወፅ ለአካባቢ ሰላም የመቆም ተግባር ማንም ሀገር ጎረቤቱ በሰላም እጦት እየተናወጸ መበልጸግ የሚችል የለም ከሚል እምነት የሚፈልቅ አቋም ነው ሲሉም ገልጸዋል።

ሀገራት ከግጭት ይልቅ ትብብርን ሲመርጡ ምን ያህል ማሳካት እንደሚችሉ ተመልክተናል በማለት ገልጸው፤ ስለሆነም አፍሪካውያን ለሰላማችን ኃላፊነቱን በመውሰድ እና በቅንጅት ለጋራ ሰላም መሥራት አለብን ብለዋል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ የ13 ሀገራት ተወካዮች የአፍሪካ ኅብረት ተወካዮች፣ ዲፕሎማቶች እና የተቋማት ተወካዮች የሚሳተፉበት የሶስት ቀናት ቀጣናዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

በለይኩን ዓለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.