Fana: At a Speed of Life!

በትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይዎት አለፈ  

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሸነን ዱጎ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይዎት ማለፉ ተገለጸ፡፡

ከሟቾች በተጨማሪ በ25 ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ፋሪድ ይሳቅ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል፡፡

አደጋው የተከሰተው፤ በተለምዶ አይሱዙ ተብሎ የሚጠራው የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ 42 ሰዎችን ከተለያዩ ሸቀጦች ጋር ጭኖ ከዋልዳያ ከተማ ወደ መሰላ ወረዳ በመጓዝ ላይ ሳለ በመገልበጡ ነው ብለዋል፡፡

በፀሐይ ጉሉማ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.