Fana: At a Speed of Life!

ከ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር በላይ የኢንቨስትመንት ስምምነቶች ተፈረሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ 2025 ፎረም ላይ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር በላይ የኢንቨስትመንት ስምምነቶችን ተፈራረመ፡፡

ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ 2025 ፎረም ዛሬ ተጠናቅቋል፡፡

በፎረሙ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ለኢንቨስትመንት በቁርጠኝት እየሠራ መሆኑ በስፋት መነሳቱ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ በግብርናና አግሮፕሮሰሲንግ፣ በማምረቻ፣ በአገልግሎት፣ በአይሲቲ እና በሌሎችም ዘርፎች ከፍተኛ አቅም እንዳላት ያሳየችበት መድረክ መሆኑን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) አስታውቀዋል፡፡

በሀገሪቱ የተወሰዱ የኢኮኖሚ ሪፎርሞችም ለኢንቨስትመንት ዘርፉ ወሳኝነት ያላቸው መሆኑን አብራርተዋል።

በታምራት ደለሊ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.