Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል አሲዳማ አፈርን በማከም ምርታማነትን ለመጨመር እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል አሲዳማ አፈርን በኖራ በማከም ምርታማነትን ለመጨመር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል፡፡

በቢሮው የአፈር ለምነትና ማሻሻያ ዳይሬክተር እሸቱ ለገሰ÷ በግብርና ዘርፍ ምርታማነትን ከሚቀንሱ ተግዳሮች ውስጥ የአፈር በአሲዳማነት መጠቃት አንዱ ነው፡፡

አሁን ላይ በኦሮሚያ ክልል 2 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት በአሲዳማነት የተጠቃ መሆኑን ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

በአሲዳማነት የተጠቃን አፈር ለማከምና ምርታማነቱን ለመጨመርም በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

በዚህ መሰረትም ጉደር በሚገኘው የግብርና ኖራ ፋብሪካ 193 ሺህ በላይ ኩንታል ኖራ በማምረት ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱን ተናግረዋል፡፡

ኖራውን አርሶ አደሩ በተገቢ ሁኔታ እንዲጠቀም በዞኖችና ወረዳዎች የግብርና ባለሙያዎች አስፈላጊውን ክትትል እያደረጉ እንደሚገኙ አስገንዝበዋል፡፡

አርሶ አደሩ መሬቱ አሲዳማ ከሆነና በኖራ ካልታከመ ዘር በሚዘራበት ወቅት አሲዳማ አፈርን መቋቋም የሚችሉ ሰብሎችን እንዲጠቀም የግንዛቤ መፍጠር ሥራ መሰራቱንም አንስተዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.