ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ለተከታታይ 3ኛ ዓመት የዓለማችን ቁጥር አንድ ተከፋይ ስፖርተኛ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ40 ዓመቱ ፖርቹጋላዊ ኢንተርናሽናል ለተከታታይ ለሦስተኛ ዓመት የዓለማችን ቁጥር አንድ ተከፋይ ስፖርተኛ መሆን ችሏል፡፡
በአሁኑ ወቅት ለሳዑዲው ክለብ አልናስር እየተጫወተ የሚገኘው ክሪስቲያኖ ሮናልዶ፤ በዓመት 275 ሚሊየን ዶላር የሚከፈለው የምድራችን ቁጥር አንድ ስፖርተኛ መሆኑን የፎርብስ መጽሔት መረጃ አመላክቷል፡፡
አሜሪካዊው የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ስቴፈን ከሪ 156 ሚሊየን ዶላር ዓመታዊ ገቢ በማግኘት ሁለተኛ እንዲሁም የከባድ ሚዛን ቦክሰኛው ታይሰን ፉሪ በ146 ሚሊየን ዶላር ዓመታዊ ገቢ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
በሌላ በኩል አርጀንቲናዊው የኢንተር ሚያሚ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ 135 ሚሊየን ዶላር ዓመታዊ ክፍያ በማግኘት 5ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡን የዘገበው ዘ አትሌቲክ ነው፡፡
በአቤል ንዋይ