Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ መልካም ተሞክሮ የሚቀሰምባት ሀገር ናት- የአፍሪካ ሀገራት የሐይማኖት አባቶች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የሐይማኖት አብሮነት ያላት መልካም ተሞክሮ የሚቀሰምባት ሀገር ናት ሲሉ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የሐይማኖት አባቶች ተናገሩ።

የሐይማኖት አባቶቹ ለአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 ዕቅድ መሳካት፤ ይህንን ለዘመናት የዘለቀ ዕሴት በአህጉሩ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ናይጄሪያዊው የሐይማኖት ሰላም አምባሳደር ጄምስ ሞዴልውዬ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ ብዝኀ ሐይማኖቶች ተከባብረውና ተፈቃቅደው የሚኖሩባት ተምሳሌታዊ ሀገር ናት ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የጋራ ብልጽግና ሀገራት የሐይማኖት ሰላም አምባሳደር ኢማም መሀመድ ኑሬ አልሸፋ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ አህጉር በቀል የሐይማኖት እና ባህል ዕውቀቶችን መዋቅራዊ አሥተዳደር ቅርስ መስጠት የኢትዮጵያ ሌላኛው መገለጫ ነው ብለዋል፡፡

በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ለሰላምና መረጋጋት ትልቅ ቦታ በመስጠት ሰላም ሚኒስቴር አቋቁማ መሥራቷን አድንቀዋል፡፡

የሐይማኖት አባቶቹ አፍሪካ ያሏትን የሰላምና መረጋጋት አህጉር በቀል ዕሴቶች ከሐይማኖት ጋር በመቀመር መሥራት እንዳለባት መክረዋል፡፡

በእዮናዳብ አንዱዓለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.