ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለስራ ጉብኝት ፈረንሳይ ፓሪስ ገቡ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ልዑክ ጋር በመሆን ለስራ ጉብኝት ዛሬ ፈረንሳይ ፓሪስ ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓሪስ ሲደርሱ በብሔራዊው የጦር ኃይሎች ሙዚየም የአቀባበል ሥነ ሥርዓት ተደርጎላቸዋል።
በጉብኝታቸውም ወቅት ከፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።