Fana: At a Speed of Life!

እድሳት የተደረገለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) እድሳት ሲደረግለት የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም በዛሬው ዕለት ተመርቋል።

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው (ረ/ፕ) ሙዚየሙ በ1965 ዓ.ም እንደተገነባ አስታውሰው÷ የዕድሳት ሥራው ከታኅሣሥ ወር ጀምሮ ሲከናወን መቆየቱን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል።

በእድሳቱ ግቢውን ማስተካከል እና ማስዋብ እንዲሁም ችግር ያለባቸው የውሃ መውረጃዎችን መጠገንና ማስተካከል ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

በሙዚየሙ ቋሚ የቅርስ ማሳያዎችን ማዘመን፣ ደህንነታቸውን ማስጠበቅ እና የዐውደ ርዕይ ክፍሎችን የማመቻቸት ስራ መሰራቱንም አንስተዋል።

ለሙዚየሙ እድሳት እና ማስዋብ የፈረንሳይ መንግስት በገንዘብና ቁሳቁስ እንዲሁም የሙያ ድጋፍ ማድረጉን ገልጸው÷ ከነገ ጀምሮ ለሕዝብ ክፍት እንደሚደረግ ተናግረዋል።

በስንታየሁ አበበ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.