Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ቡና ኢትዮጵያ መድንን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ31ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድንን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የኢትዮጵያ ቡናን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ራምኬል ጀምስ በመጀመሪያው አጋማሽ ከመረብ አሳርፏል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና ማሸነፉን ተከትሎ ከሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ስድስት ዝቅ ማድረግ ችሏል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና ባለፉት አምስት የሊጉ ጨዋታዎች ድል ሲያደርግ ኢትዮጵያ መድን ከሁለት ተከታታይ ጨዋታ ድል በኋላ ሽንፈት አስተናግዷል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ መድን በ60 ነጥብ ሊጉን እየመራ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና በ54 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.