Fana: At a Speed of Life!

ግራቨንበርች- የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጨዋች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሊቨርፑል የመሐል ሜዳ ተጨዋች ግራቨንበርች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2024/25 የውድድር ዘመን የዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጨዋች በመባል ተመርጧል፡፡

የ23ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ግራቨንበርች ከእንግሊዛዊው ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ ቀጥሎ የዓመቱ ወጣት ተጨዋች ሽልማትን ያሸነፈ 2ኛው የሊቨርፑል ተጨዋች ሆኗል፡፡

ኔዘርላንዳዊው ግራቨንበርች በዚህ የውድድር ዓመት በሊጉ ባደረጋቸው 36 ጨዋታዎች አራት ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል፡፡

በወንድማገኝ ጸጋዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.