Fana: At a Speed of Life!

ሲዳማ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ31ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የሲዳማ ቡናን የማሸነፊያ ግብ ብርሃኑ በቀለ በመጀመሪያው አጋማሽ ከመረብ አሳርፏል፡፡

ሲዳማ ቡና ተከታታይ ሦስተኛ ድሉን ሲያሳካ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ባለፉት ሦስት ተከታታይ ጨዋታዎች ተሸንፏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ሲዳማ ቡና በ46 ነጥብ 4ኛ እንዲሁም ቅዱስ ጊዮርጊስ በ40 ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል ምሽት 12 ሠዓት ላይ ሀድያ ሆሳዕና ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.