ሰንደርላንድ ዳግም ወደ ፕሪሚየር ሊግ አደገ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለማደግ በተደረገ የጥሎ ማለፍ የፍፃሜ ጨዋታ ሰንደርላንድ ሼፊልድ ዩናይትድን 2 ለ 1 በማሸነፍ ከሻምፒዮን ሺፕ ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማደጉን አረጋጧል፡፡
ዌምብሌይ ስታዲየም ላይ በተደረገው የጥሎ ማለፍ የፍፃሜ ጨዋታ፤ ሰንደርላንድን ወደ ሊጉ ማሳደግ የቻሉትን ግቦች ማዬንዳ እና ቶም ዋትሰን ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
እንዲሁም የሼፊልድ ዩናይትድን ብቸኛ ግብ ካምቤል በመጀመሪያው አጋማሽ ማስቆጠር ችሏል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ሰንደርላንድ በሚቀጥለው የውድድር ዓመት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
በተመሳሳይ፤ በርንሌይ እና ሊድስ ዩናይትድ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ማደጋቸውን ቀደም ብለው ማረጋገጣቸው ይታወሳል፡፡