Fana: At a Speed of Life!

የስፖርት ቱሪዝምን ለማነቃቃት እየተሰራ ነው – ሰላማዊት ካሳ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቱሪዝም ሚኒስቴር ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት አራተኛው ቦቆጂ የ’ልወቅሽ ኢትዮጵያ’ የ12 ኪ.ሜ የሩጫ ውድድር ዛሬ ተካሂዷል።

በውድድር መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ቦቆጂ የ’ልወቅሽ ኢትዮጵያ’ ሩጫ ውድድር በዋነኛነት አካባቢውን በማስተዋወቅ፣ ያለውን ትሩፋት በማሳየት ከስፖርት ቱሪዝም ተጠቃሚ ለማድረግ የሚካሄድ መሆኑን ገልጸዋል።

የቱሪዝም ሚኒስቴር ውድድሩ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካውያን እና ለጥቁር ህዝቦች በሙሉ ኩራት የሆኑ አትሌቶችን ባፈራችው ከተማ ውስጥ በመካሄዱ ኩራት ይሰማዋል ብለዋል።

የቦቆጂ ምድር በዓለም አደባባይ ላይ በአትሌቲክሱ ዘርፍ የነገሱ ታላላቆችን ማፍራት የቻለች ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ትርጉም ያላት ድንቅ ከተማ ናት ሲሉ ገልጸዋል።

በቦቆጂ ከተማ እና አካባቢዋ የሚደረጉ የቱሪዝም እንቅስቃሴዎች ማህበረሰቡን ተጠቃሚ እንዲያደርጉ መስራት እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።

የስፖርት ቱሪዝምን በመላ ሀገሪቱ ለማነቃቃት በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ገልጸው፤ በተለይም ደግሞ ‘ልወቅሽ ኢትዮጵያ’ ሀገራችንን እንድናውቅ እድል የሚሰጠን ነው ብለዋል።

በአራተኛው ቦቆጂ የ’ልወቅሽ ኢትዮጵያ’ የ12 ኪ.ሜ የሩጫ ውድድር በሴቶች አትሌት መሰረት ጣፋ እንዲሁም በወንዶች አትሌት ስዩም ድሪባ አሸንፈዋል።

በዮናስ ጌትነት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.